ዓባይ ባንክ ለባንኩ ሰባተኛ የሆነውን ቀጠና ፅ/ቤት (ዲስትሪክት) በታላቋ ጎንደር ከተማ በደማቅ ሁኔታ በመክፈት አስመረቀ፡፡

ባንኩ የደንበኞችን ተደጋጋሚ ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በጎንደር እና አካባቢዉ ያሉትን የባንኩን ቅርንጫፎች አቅም በማጎልበት ደንበኞችን በቅርበት ማገልገል እንዲቻል፣ “ጎንደር ዲስትሪክት” በሚል ስያሜ የዲስትሪክት ቢሮ በጎንደር ከተማ መክፈቱን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡

የጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ፣ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣  የስራ አመራር አባላት እና  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጎንደር ከተማ በተካሄደ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ስራውን በይፋ  ጀምሯል፡፡

 

ዓባይ፣ ታማኝ አገልጋይ !

Leave a Reply

Your email address will not be published.