በዓባይ ባንክ በኩል የፐብሊክ ባስ ትራንስፖርት ክፍያ መፈጸም ተጀመረ

በዓባይ ባንክ በኩል የፐብሊክ ባስ ትራንስፖርት ክፍያ መፈጸም ተጀመረ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. እና ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት አድርገዋል፡፡

ስምምነቱ የአገር አቋራጭ የጉዞ ትኬት ክፍያን በዓባይ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በቅርንጫፎች በኩል በሂሳብ ወይም በጥሬ ገንዘብ መፈጸም የሚያስችል ነው፡፡

በዚህ መሰረት አገልግሎቱ መነሻውን ከአዲስ አበባ በማድረግ ወደ ባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ ሚዛን ተፈሪ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ባሌ ሮቤ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋ ከተሞች የተሟላ የፐብሊክ ባስ የጉዞ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.