ዓባይ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገንዘብ ድጋፍና የምሳ ግብዣ ፕሮግራም አካሂዷል።

ዓባይ ባንክ የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከምሳ ግብዣው በተጨማሪ የ2,111,810.00 (ሁለት ሚሊየን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ስምንት መቶ አስር ብር) የገንዘብ ድጋፍ እና ከባንኩ ሠራተኞች የተሰበሰቡ አልባሳትን አቶ የኋላ ገሠሠ ለማዕከሉ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ አስረክበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ማዕከሉን ጎብኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.