ዓባይ ባንክ ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ “ይገምቱ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ

ዓባይ ባንክ ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ “ይገምቱ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ “ይገምቱ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ሥነ – ሥርዓት ዛሬ አከናውኗል፡፡

በውድድሩ የሩብ ፍጻሜ፣ ግማሽ ፍጻሜ እና ፍጻሜ ጨዋታዎች ትክክለኛ ውጤት በባንኩ የፌስቡክ ገጽ መልዕክት መቀበያ (inbox) ቀድመው በመላክ ለገመቱ አሸናፊዎች ከ2ሺህ ብር እስከ 12ሺህ ብር መጠን ያለው የዓባይ  ባንክ ኤቲኤም ካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ 

አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን ከዓባይ ባንክ የማርኬቲንግ እና ሪሰርች ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ክርስቲያን ካሣ ተቀብለዋል፡፡

አሸናፊዎቹ ባንኩ ቃሉን ጠብቆ ሽልማቱን በማበርከቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.