ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. በዋግ ኸምራ እና በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ የሚውል የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ በዛሬው ዕለት አደረገ።

ድጋፉን አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር አስረክበዋል፡፡

ዓባይ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን ተከስተው ለነበሩ ማኅበራዊ ቀውሶች ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ሲያሳይ መቆየቱን የሚታወስ ሲሆን፤በቀጣይም በአገራችን ለሚከሰቱ መሰል ችግሮች ድጋፍ በማድረግ ተቋማዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አቶ የኋላ አስታውቀዋል፡፡

ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ በበኩላቸው ዓባይ ባንክ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር በየጊዜው ንቁ ተሳትፎ እያደረገ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በድርጅታቸው በኩል በፍጥነት እንደሚደርስ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.