ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሥራ ስምምነት ውል ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሥራ ስምምነት ውል ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከሳፋሪኮም ኤምፔሳ ጋር ስትራቲጂክ የሥራ አጋር በመሆን አብረው ለመሥራት  የሥራ  ስምምነት ውል ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱም መሰረት ዓባይ ባንክ የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ሱፐር ኤጀንት በመሆን የሞባይል ባንኪንግ እና የኤጀንት ባንኪንግ ሥራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማሳለጥ እንዲሁም ደንበኞች ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ወደ ኤምፔሳ ሒሳባቸው ወይም ከኤምፔሳ ሒሳባቸው ወደ ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሒሳብ መረጃዎችን እንዲያዩ፣ የአየር ሰዓት እንዲገዙ እና ሌሎችንም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው፡፡

በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠና የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፖል ካቫቩ በሰጡት አስተያየት የተጀመረውን የሥራ አጋርነት ስምምነት በማጠናከር ደንበኞችን የዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እና የክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.