ዓባይ ባንክ እና የፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና የፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን አቶ አቡበከር ነዚር የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት  ተጠባባቂ ምክትል ዋና መኮንን እና ዶ/ር አሚን መሐመድ አሊ የሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ተፈራርመዋል፡፡ 

በስምምነቱ መሰረት ባንኩ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቱና ለመስጅዶች መስጠት ያስችለዋል።

በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ እንደተጠቀሰው በክፍለከተማው ውስጥ የሚገኙ መስጅዶች ገቢያቸውን በተደራጀ ሁኔታ ለመሰብሰብን ጨምሮ ባንኩ በሚሰጠው ሰዲቅ – ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አግልግሎቶችን ለመሥራት የሚያስችል እንደሆነ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.