ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ሰጠ

ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ሰጠ

ዓባይ ባንክ ለሁለት ቀናት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ በ2021/22 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡

የባህርዳር ቀጠና ጽሕፈት ቤት ባስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም የአንደኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን፣ የአዝዋ፣ አምደወርቅ፣ አራትኪሎ፣ ቋራ እና ስታዲየም ቅርንጫፎች የእውቅና ሰርተፊኬት እና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የደሴ ቀጠና ጽሕፈት ቤት በሀገራችን ተከስቶ የነበረውን ችግር ተቋቁሞ በችግሩ አካባቢ ያሉትን የባንኩ ቅርንጫፎች በፍጥነት ወደነበሩበት ቁመና ተመልሰው የተሟላ የባንክ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ በትጋት ባከናወነው ሥራ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የበጀት ዓመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.