ዓባይ ባንክ የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ

ዓባይ ባንክ የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ

ዓባይ ባንክ እየሰራበት የሚገኘውን ስትራቴጂ ዕቅድ በማጠናቀቅ ከ2023/24- 2027/28 ቀጣይ አምስት ዓመታት የሚገለገልበትን ስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መድረክ አካሂዷል፡፡

የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡  

አቶ የኋላ በመድረኩ እንደገለጹት ስትራቴጂ ዕቅዱ ዓባይ ባንክ ጊዜው የሚጠይቀውን የደንበኞቹን ፍላጎት በተሻለ መልክ ለሟሟላት የሚያስችል የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ይበልጥ በባንክ ኢንደስትሪው ተወዳዳሪና መሪ ባንክ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡  

ዓባይ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋፋት በመላ ሀገሪቱ የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ400 በላይ ያደረሰ ሲሆን፣ በኢንተርኔትና ሞባይል ባንኪንግ ዘርፈ ብዙ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ ደንበኞቹን እያገለገለ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.ኤ ሰኔ 30/2022 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 3.9 ቢሊየን ብር ሲሆን አጠቃላይ ሀብቱ  40 ቢሊየን ብር በላይ ደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.