ዓባይ ባንክ፣ የኢትዮጵያ መድሐኒት ፋብሪካ እና ሜድቴክ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ፣ የኢትዮጵያ መድሐኒት ፋብሪካ እና ሜድቴክ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ፣ የኢትዮጵያ መድሐኒት ፋብሪካ አ.ማ. (ኢመፋ) እና ሜድቴክ ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ ማህበር በዓባይ ሰዲቅ – ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን በመጠቀም በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር አቶ አቡበከር ነዚር፣ የኢመፋ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ማሙዬ እና የሜድቴክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ንጉሴ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የኢመፋ እና የሜድቴክ ሠራተኞች በዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የሰራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያዎችን በዓባይ ባንክ በኩል ለመፈፀም የሚያስችል አገልግሎቶችን እንደሚያካትት ታውቋል፡፡

ዓባይ ባንክ የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሰራሮችን መሰረት አድርጎ ባዘጋጀው ሰዲቅ – ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.