ዓባይ ባንክ በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት “ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ” በመባል የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀዉ የእውቅና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ባንካችን ለሀገራችን ከፍተኛ ግብር በታማኝነት እና በሀቀኝነት በመክፈሉ የፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ዓባይ ባንክ የሀገር እና የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡