ዓባይ ባንክ እና ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21/2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሠ አሰፋ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ሠራተኞች የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው የአቡነ ጎርገጎርዮስ ትምህርት ቤት የተማሪዎችን ወርሃዊ ክፍያ በዓባይ ባንክ በኩል መሰብሰብ የሚያስችል አሰራርን መዘርጋቱ በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከዳሽን ቢራ አ.ማ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋግ ልማት ማህበር፣ ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል፣ ኑር ኢንተርናሽናል፣ አይኤፍ ዓለምአቀፍ የማዳበሪያ ልማት ማዕከል እና ከሌሎችም ድርጅቶች ጋር የብድር አገልግሎት በመስጠት ሠራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.