ዓባይ ባንክ የሥትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት ቡድን የምክክር መድረክ አካሄደ

ዓባይ ባንክ የሥትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት ቡድን የምክክር መድረክ አካሄደ

የዓባይ ባንክ የትራቴጂክ ልማት ቴክኒካል ቡድን በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ለስምንት ቀናት የስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት የምክክር ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ እና ማርኬቲንግ ዋና መኮንን በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያዘጋጀው የስትራቴጂ ዕቅድ በሀገሪቱ ያለውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ፈጣን ዕድገት፣ የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል፣ ዘመኑን የሚዋጅ፣ ተፎካካሪ እና ውጤታማ የሆነ የስትራቴጂ ዕቅድ  እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡    

በፕሮግራሙ መጠናቀቂያ ላይ የኃይሌ ግራንድ ሆቴል የባንኩ አባላት በሆቴሉ ለነበራቸው ቆይታ የምስጋና ፕሮግራም ያዘጋጁ ሲሆን፣ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ ሆቴሉ ለሰጠው ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በዓባይ ባንክ እና በቴክኒካል ቡድኑ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.