ዓባይ ባንክ እና አፍራ አስመጪና ላኪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና አፍራ አስመጪና ላኪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከአፍራ አስመጪና ላኪ ኃ.የተ.የግ.ማኅበር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ተጠባባቂ ምክትል ዋና መኮንን አቡበከር ነዚር እና ከአፍራ አስመጪና ላኪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ካሊድ ሳሌህ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ባንኩ በሚሰጠው ሰዲቅ -ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል በበርካታ የፋይናንስ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችል እንደሆነ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ለመስጠት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ዘርፈ ብዙ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.