የደሴ ከተማ አስተዳደር ከዓባይ ባንክ ባገኘው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎችን ተረከበ

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከዓባይ ባንክ ባገኘው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎችን ተረከበ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የደሴ ከተማ አስተዳደር የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ ለከተማ አሰተዳደሩ በሰጠው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎች/ማሽኖች/ የከተማ አስተዳደሩ መረከቡን አስታውቋል፡፡

የዓባይ ባንክ አ.ማ. ደሴ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ተስፋዬ የማሽኖቹ ርክክብ በተካሄደበት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ዓባይ ባንክ ለደሴ ከተማ አስተዳደር ብድር በመስጠት የመንገድ ግንባታ ማሽኖች መግዛት ማስቻሉ ባንኩ የልማት ሥራዎችን በፋይናንስ አቅርቦት እየደገፈ እና ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ባንኩ ለንግዱ ማህበረሰብ፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የብድር አቅርቦት በመስጠት አጋርነቱን እያስመሰከረ መሆኑን አቶ ዮናስ አክለው ጠቅሰዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ እሸቱ በበኩላቸው ዓባይ ባንክ ብድሩን በመፍቀድ የልማት አጋርነቱን በተግባር ማረጋገጥ በመቻሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.