ዓባይ ባንክ አ.ማ በባሕር ዳር መሰናዶ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ውሃ ማጣሪያ ግንባታ አሰርቶ ለትምህርት ቤቱ አስረከበ፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የባንኩ የባሕር ዳር ቀጠና ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ጸጋዬ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ስራዎችን በስፋት እየሰራ መሆኑን አንስተው÷ በባሕር ዳር መሰናዶ ትምህርት ቤት የተደረገውም ግንባታ የዚሁ...
Category: <span>ዜና</span>
ዓባይ ባንክ ለ6ኛ ዙር ያዘጋጀው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ
ዓባይ ባንክ አ.ማ የ6ኛ ዙር “የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት የካቲት 17/2015 ዓ.ም በኃይሌ ግራድ አዲስ አበባ ሆቴል አከናውኗል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኃላ ገሠሠ የፕሮግራሙ ዋና አላማ የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማጎልበትና በባንኩ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት በመጠቀም ህጋዊ የገንዘብ ምንዛሬን ለማበረታታት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ሰዓት...
የዓባይ ባንክ የስራ አመራርና ሠራተኞች ደም ለገሱ
የዓባይ ባንክ አ.ማ. ተቋማዊ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህን ተሳትፎውን ይበልጥ ለማጎልበት የባንኩ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በባንኩ ዋና መ/ቤት በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲውል ለብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የደም ልገሳ አካሂደል፡፡ ዓባይ ባንክ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት እንዲቻል ለወገኖችና ተቋማት ትርጉም ያለው ድጋፍ በማድረግና ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ...
የዓባይ ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
ዓባይ ባንክ ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 19/2015 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ እና ማርኬቲንግ ዋና መኮንን እንደተናገሩት የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ...
ዓባይ ባንክ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ውይይት አደረገ
የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የስራ አመራሮች የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም በሀይሌ አዲስ አበባ ሆቴል ውይይት አድርገዋል፡፡በውይይቱ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ የባንኩ የ2015 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀም የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ በቀሪዎቹ የበጀት ዓመቱ ጊዜያት በገበያው ያለውን ዕድል መጠቀም እንዲቻልና በበጀት ዓመቱ የተቀመጠውን...
ዓባይ ባንክ ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ “ይገምቱ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ
ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ “ይገምቱ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ሥነ – ሥርዓት ዛሬ አከናውኗል፡፡ በውድድሩ የሩብ ፍጻሜ፣ ግማሽ ፍጻሜ እና ፍጻሜ ጨዋታዎች ትክክለኛ ውጤት በባንኩ የፌስቡክ ገጽ መልዕክት መቀበያ (inbox) ቀድመው በመላክ ለገመቱ አሸናፊዎች ከ2ሺህ ብር እስከ 12ሺህ ብር መጠን ያለው የዓባይ ባንክ ኤቲኤም ካርድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን ከዓባይ ባንክ...
ዓባይ ባንክ በገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር በመሳተፍ ላይ ይገኛል
ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2015 የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ባንካችን ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡ በኤግዚቢሽን ማዕከልና ዲሲቲ ኢንተርቴይንመንት አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ታኅሣሥ 28/2015 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
ዓባይ ባንክ የሥትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት ቡድን የምክክር መድረክ አካሄደ
የዓባይ ባንክ የትራቴጂክ ልማት ቴክኒካል ቡድን በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ለስምንት ቀናት የስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት የምክክር ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ እና ማርኬቲንግ ዋና መኮንን በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያዘጋጀው የስትራቴጂ ዕቅድ በሀገሪቱ ያለውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ፈጣን ዕድገት፣ የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል፣ ዘመኑን የሚዋጅ፣ ተፎካካሪ እና ውጤታማ...
ዓባይ ባንክ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጤት በመገመት ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር አዘጋጀ
ዓባይ ባንክ አ.ማ. በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጋር በተገናኘ በባንኩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ጥያቄዎችን በማቅረብ ትክክለኛውን ውጤት በመገመት የሚያሸልም ውድድር አዘጋጅቷል፡፡ በውድድሩ የሩብ ፍጻሜ፣ ግማሽ ፍጻሜ እና የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ቀድመው ውጤቱን በትክክል የገመቱ ተሳታፊዎች ተሸላሚ የሚሆኑ ሲሆን፣ አሸናፊዎቹ ከ2ሺህ ብር እስከ 12 ሺህ ብር መጠን ያለው የዓባይ ባንክ ካርድ ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡ ተሳታፊዎች ግምታቸውን...
የዓባይ ባንክ ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን አከበሩ
የዓባይ ባንክ አ.ማ. ሠራተኞች በየዓመቱ ህዳር 30 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በግራንድ ፓላስ ሆቴል በፓናል ውይይት አክብረዋል።