Category: <span>ማስታወቂያ</span>

ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
Post

ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዓበይ ባንክ አ.ማ. በዋግ ኸምራ እና በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ የሚውል የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ በዛሬው ዕለት አደረገ። ድጋፉን አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር አስረክበዋል፡፡ ዓባይ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን ተከስተው ለነበሩ ማኅበራዊ ቀውሶች ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ሲያሳይ...

ዓባይ ባንክ “ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ” የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት
Post

ዓባይ ባንክ “ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ” የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት

ዓባይ ባንክ በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት “ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ” በመባል የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀዉ የእውቅና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ባንካችን ለሀገራችን ከፍተኛ ግብር በታማኝነት እና በሀቀኝነት በመክፈሉ የፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ዓባይ ባንክ የሀገር እና የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

ዓባይ ባንክ 7ኛውን ዙር “ይቆጥቡ፤ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አስጀመረ
Post

ዓባይ ባንክ 7ኛውን ዙር “ይቆጥቡ፤ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም አስጀመረ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከነሐሴ 26/2015 ዓ.ም. እስከ ጥር 10/2016 ዓ.ም. የሚቆየውን 7ኛ ዙር “ይቆጥቡ፤ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ” ፕሮግራም በይፋ አስጀምሯል፡፡ ደንበኞች ከብር 250.00 ጀምረው ሲቆጥቡ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ከውጭ አገር የላኩላቸውን ገንዘብ በዓባይ ባንክ ሲቀበሉ ወይም ሲመዝሩ ተሸላሚ በሚያደርጋቸው የዕጩ ዕድለኞች ዝርዝር ውስጥ እንደሚገቡ ታውቋል፡፡ ለሽልማት የቀረቡ ዕጣዎች ዝርዝር፡-1ኛ ዕጣ፡ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል2ኛ ዕጣ፡ በርካታ ፍሪጆች3ኛ...

የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሥልጠና እና ምክክር መድረክ አካሄዱ
Post

የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሥልጠና እና ምክክር መድረክ አካሄዱ

የዓባይ ባንክ አ.ማ. የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሁለት ቀናት የሥልጠና እና የምክክር መድረክ በአምባሳደር ሆቴል አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አብዱልመናን ከበደ፣ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ኡስታዝ ባህሩ ዑመር እና የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ሼህ ሰዒድ ኪያር ተገኝተው ከታሳታፊዎች ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አቶ መሐመድ አሕመድ...

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሥራ ስምምነት ውል ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና ሳፋሪኮም ኤምፔሳ የሥራ ስምምነት ውል ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከሳፋሪኮም ኤምፔሳ ጋር ስትራቲጂክ የሥራ አጋር በመሆን አብረው ለመሥራት  የሥራ  ስምምነት ውል ተፈራረሙ፡፡ በስምምነቱም መሰረት ዓባይ ባንክ የሳፋሪኮም ኤምፔሳ ሱፐር ኤጀንት በመሆን የሞባይል ባንኪንግ እና የኤጀንት ባንኪንግ ሥራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማሳለጥ እንዲሁም ደንበኞች ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ወደ ኤምፔሳ ሒሳባቸው ወይም ከኤምፔሳ ሒሳባቸው ወደ ከዓባይ ባንክ ሒሳባቸው ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሒሳብ...

ዓባይ ባንክ የ2016 ዓ.ም. የአዲስ ዓመት ባዛር ላይ በመሳተፍ ደንበኞችን በማገልገል ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ የ2016 ዓ.ም. የአዲስ ዓመት ባዛር ላይ በመሳተፍ ደንበኞችን በማገልገል ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እና በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጁት የ2016 አዲስ ዓመት ዋዜማ ባዛር እና ኤክስፖ ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ሴንቸሪ ፕሮሞሽን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲሁም ባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ያዘጋጇቸው ሁለቱም ባዛሮች እስከ ጳጉሜን 06/2015 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ፡፡በባዛር ጉብኝትዎ ለሚያስፈልግዎ ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በዓባይ ባንክ እንዲገለገሉ ጋብዘንዎታል፡፡

ዓባይ ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎች ግዢ  ድጋፍ እያደረገ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎች ግዢ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተገናኘ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ ለከተማ አስተዳደሩ 220 ሚሊየን ብር ብድር ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በብድሩ የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎች/ማሽኖች/ ተረክቧል፡፡     የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ዓባይ ባንክ ብድሩን በመፍቀድ የልማት አጋርነቱን በተግባር ማረጋገጥ...

ዓባይ ባንክ ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ አካሄደ
Post

ዓባይ ባንክ ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ አካሄደ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የ2022/23 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ የዲስትሪክት ኃላፊዎች እና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት ከሐምሌ 7 እስከ 8/2015 ዓ.ም አካሂዷል። በተመሳሳይ ሁኔታ በአዲስ አበባም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ስብሰባው ተካሂዷል፡፡

ዓባይ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ድጋፍ አደረገ
Post

ዓባይ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተከናወነው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ላይ የስትራቴጂክ አጋር በመሆን 5,000,000.00 (አምስት ሚሊየን) ብር ድጋፍ አድርጓል። መርሐግብሩ ላይ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መምህራን፣ ዘማሪያን፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም የእምነቱ...

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከዓባይ ባንክ ባገኘው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎችን ተረከበ
Post

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከዓባይ ባንክ ባገኘው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎችን ተረከበ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የደሴ ከተማ አስተዳደር የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ ለከተማ አሰተዳደሩ በሰጠው የ200 ሚሊየን ብር ብድር የተገዙ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ መሣሪያዎች/ማሽኖች/ የከተማ አስተዳደሩ መረከቡን አስታውቋል፡፡ የዓባይ ባንክ አ.ማ. ደሴ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ተስፋዬ የማሽኖቹ ርክክብ በተካሄደበት ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ዓባይ ባንክ ለደሴ ከተማ አስተዳደር ብድር በመስጠት የመንገድ ግንባታ ማሽኖች መግዛት ማስቻሉ ባንኩ...