Category: <span>ዜና</span>

ዓባይ ባንክ አዲሱን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ
Post

ዓባይ ባንክ አዲሱን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከ2023/24-2027/28 የሚገለገልበትን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ በየደረጃው የሚገኙ የባንኩ የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ይፋ አደረገ። የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደተናገሩት ነባራዊውን የዓለምአቀፍ እና የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ ያገናዘበ፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ፈጣን ዕድገት ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል፣ ተፎካካሪ እና ውጤታማ የሆነ የስትራቴጂ ዕቅድ መዘጋጀቱን...

ዓባይ ባንክ እና አዲል ኮርፖሬት ግሩፕ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ እና አዲል ኮርፖሬት ግሩፕ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከአዲል ኮርፖሬት ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አቡበከር ነዚር እና የአዲል ኮርፖሬት ግሩፕ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አዲል አብደላ ታቢት (ፒኤችዲ) ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ ባንኩ በሚሰጠው ሰዲቅ -ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል በበርካታ የፋይናንስ...

ዓባይ ባንክ 477ኛውን ቅርንጫፍ በወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሰ ስም በመሰየም ሥራ አስጀመረ
Post

ዓባይ ባንክ 477ኛውን ቅርንጫፍ በወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሰ ስም በመሰየም ሥራ አስጀመረ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለበርካታ ዓመታት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ በቆዩት በወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሰ ስም የሰየመውን 477ኛ ቅርንጫፉን በአያት ጣፎ አካባቢ በመክፈት ሥራ አስጀምሯል። ወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሰ ዓባይ ባንክ በስማቸው ቅርንጫፍ በመሰየም ለሰጣቸው አክብሮት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዓባይ ባንክ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተደራሽነቱን በማስፋፋት ላይ ሲሆን አሁን ላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት...

ዓባይ ባንክ ነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱን በክብር ሸኘ
Post

ዓባይ ባንክ ነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱን በክብር ሸኘ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ባንኩን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ባዘጋጀው ዝግጅት ሽኝት አድርጓል። ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሠ እና ሶስት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሽኝት ተደርጎላቸዋል። በኘሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱ ለባንኩ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል። የዕለቱ የክብር...

ዓባይ ባንክ በደሴ ከተማ ለተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ድጋፍ አደረገ
Post

ዓባይ ባንክ በደሴ ከተማ ለተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የ1444ኛውን የታላቁ የረመዳን ጾም ምክንያት በማድረግ በደሴ ከተማ በተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ድጋፍ አድርጓል፡፡በዝግጅቱ ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች የታደሙ ሲሆን ፕሮግራሙ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ባንኩ ድጋፍ በማድረግ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ዓባይ ባንክ የኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ ጊዜያት ለማህበረሰቡ ትርጉም ያለው የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዓባይ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና ተሰጠው
Post

ዓባይ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና ተሰጠው

ዓባይ ባንክ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የልዩ መብት መታወቂያ የምስክር ወረቀት መጋቢት 26/2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ተቀብሏል፡፡ የልዩ መብት መታወቂያ የምስክር ወረቀቱን የዓባይ ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ አማካሪ ወ/ሮ እመቤት ስጦታው ከገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተቀብለዋል፡፡ በመርሃግብሩ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ አስመጪዎች፣ ላኪዎች፣ አምራቾች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች በአጠቃላይ 193 ከፍተኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች...

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የትንሣዔ ባዛር ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የትንሣዔ ባዛር ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ የ2015 ዓ.ም የትንሣዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ባዛር ላይ በመሳተፍ ለጎብኝዎችና ለተሳታፊዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የባዛሩ ታዳሚ ደንበኞች የሚያስፈልጋቸውን የባንክ አገልግሎቱን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡  ዓባይ ባንክ ለደንበኞች አመቺ በሆኑ ጊዜ እና ቦታዎች ላይ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ሲሆን÷...

ዓባይ ባንክ በኤግዚቢሽን ማዕከል የትንሣዔ ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በኤግዚቢሽን ማዕከል የትንሣዔ ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ የ2015 ዓ.ም የትንሣዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ባንካችን ለጎብኝዎችና ለተሳታፊዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡በሴንቸሪ ፕሮሞሽን “ሰላም ፋሲካ-ኤክስፖ 2023” በሚል ተዘጋጅቶ በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ሚያዚያ 07/2015 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ዓባይ ባንክ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱን የዓባይ ባንክ የባሕር ዳር ቀጠና ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሳይ ጸጋዬ እና የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ሰጥዬ ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የቤትና የመኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በመስፋፋት ደንበኞቹን...